የምሥራቁ በር ጠባቂ የሆነው የሌዋዊው የዪምና ልጅ ቆሬ ደግሞ ለእግዚአብሔር በቀረበው የበጎ ፈቃድ ስጦታ ላይ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትንም ነገሮች ለማከፋፈል፣ ኀላፊ ነበረ።
ዘሌዋውያን 2:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተረፈውም የእህሉ ቍርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ቍርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእህሉም ቁርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለጌታ በእሳት ከቀረበው የቁርባን ክፍል በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀሪው መባ ግን ለካህናቱ ይሰጥ፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ ተከፍሎ የተወሰደ በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመሥዋዕቱም የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ከእግዚአብሔር መሥዋዕት የተረፈ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእህሉም ቍርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የሚሆን የእሳት ቍርባን ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። |
የምሥራቁ በር ጠባቂ የሆነው የሌዋዊው የዪምና ልጅ ቆሬ ደግሞ ለእግዚአብሔር በቀረበው የበጎ ፈቃድ ስጦታ ላይ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትንም ነገሮች ለማከፋፈል፣ ኀላፊ ነበረ።
እርሱም፣ “ይህ ስፍራ ሕዝቡን ለመቀደስ መሥዋዕቱን ወደ ውጩ አደባባይ እንዳያወጡ፣ ካህናቱ የበደሉን መሥዋዕትና የኀጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፣ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ቦታ ነው” አለኝ።
ሙሴም አሮንንና የተረፉትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው የእህል ቍርባን የቀረውን ወስዳችሁ ቂጣ ጋግሩ፤ እጅግ ቅዱስ ስለ ሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት።
ጠቦቱንም፣ የኀጢአት መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት በተቀደሰው ስፍራ ይረደው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱ ለካህኑ እንደሚሰጥ ሁሉ የበደል መሥዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፤ ይህም እጅግ የተቀደሰ ነው።
ሰውየው ከእነዚህ በአንዱ ኀጢአት ቢሠራ፣ ካህኑ በዚህ ሁኔታ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል። ከመሥዋዕቱ የተረፈውም እንደ እህል ቍርባን ሁሉ ለካህኑ ይሆናል።’ ”
“አሮንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ስለሚቃጠለው መሥዋዕት አቀራረብ የምትከተለው ሥርዐት ይህ ነው፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት ሌሊቱን ሁሉ እስኪነጋ ድረስ በመሠዊያው ላይ ባለው ማንደጃ ላይ ይቀመጥ፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ሲነድድ ይደር።
ለእኔ ከሚቀርብልኝ እጅግ ከተቀደሰው መባ ሁሉ፣ በእሳት የማይቃጠለው የራስህ ድርሻ ይሆናል፤ እጅግ የተቀደሰ አድርገው ከሚያመጡልኝ ስጦታ ከእህል ቍርባንም ሆነ ከኀጢአት ወይም ከበደል መሥዋዕት የሚነሣው ሁሉ የአንተና የልጆችህ ድርሻ ነው።
የእኔ ካህን እንዲሆን፣ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፣ ዕጣን እንዲያጥን፣ በፊቴም ኤፉድ እንዲለብስ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ አባትህን መረጥሁት። ደግሞም እስራኤላውያን በእሳት የሚያቀርቡትን ቍርባን ሁሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።