ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቈዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኵዝ የሚሄድ ዐንካሳ፣ ወይም በሰይፍ ተመትቶ የሚወድቅ ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ ከኢዮአብ ቤት አይታጣ።”
ዘሌዋውያን 15:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብላችሁ ንገሯቸው፤ ‘ማንም ሰው ከሰውነቱ ፈሳሽ ነገር ቢወጣ ያ ሰው ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ ማንም ሰው ከሰውነቱ ውስጥ ፈሳሽ ነገር ቢወጣ፥ ከእርሱ የሚወጣው ፈሳሽ ርኩስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው ከአባለ ዘሩ የሚወጣ ፈሳሽ ቢኖርበት፥ ያ ፈሳሽ ነገር ርኩስ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ ከሰውነቱ ዘር የሚፈስሰው ሰው ቢኖር ስለሚፈስሰው ነገር ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ ማንም ሰው ከሥጋው ፈሳሽ ነገር ቢወጣ፥ ስለሚፈስሰው ነገር ርኩስ ነው። |
ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቈዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኵዝ የሚሄድ ዐንካሳ፣ ወይም በሰይፍ ተመትቶ የሚወድቅ ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ ከኢዮአብ ቤት አይታጣ።”
“ ‘ከአሮን ዘር ተላላፊ የቈዳ በሽታ ያለበት ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ማንኛውም ሰው እስኪነጻ ድረስ ቅዱሱን መሥዋዕት አይብላ፤ እንዲሁም በአስከሬን የረከሰውን ነገር ወይም የዘር ፈሳሽ ያለበትን ሰው ቢነካ፣
“ተላላፊ የቈዳ በሽታ ያለበትን ወይም ማንኛውም ዐይነት ፈሳሽ ከሰውነቱ የሚወጣውን ወይም ሬሳ በመንካቱ በሥርዐቱ መሠረት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር እንዲያስወጡ እስራኤላውያንን እዘዝ፤