ኢያሱ 22:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ ፊንሐስና የእስራኤላውያን የጐሣ መሪዎች የነበሩት የማኅበረ ሰቡ አለቆች የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ወገኖች ያሉትን በሰሙ ጊዜ ተደሰቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ነገድ አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃላት በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ ፊንሐስና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝቡ የላካቸው የምዕራብ ነገዶች የቤተሰብ አለቆች የሆኑት ታላላቅ ሰዎች፥ የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ በሚኖሩ የምናሴ ነገዶች ሕዝብ የተናገሩትን ሰምተው መልሱ አረካቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት የእስራኤል መሳፍንት ሁሉ ፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፤ ደስም አሰኛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል አእላፋት አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው። |
ይህን በሰሙ ጊዜም የሚሉትን አጥተው እንዲህ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ “ይህማ ከሆነ አሕዛብም ወደ ሕይወት ይመጡ ዘንድ፣ እግዚአብሔር ንስሓን ሰጥቷቸዋል ማለት ነዋ።”
“በማደሪያው ድንኳን ፊት ካለው ከእግዚአብሔር ከአምላካችን መሠዊያ ሌላ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለእህል ቍርባን እንዲሁም ለሌላ መሥዋዕት ማቅረቢያ የሚሆን መሠዊያ በመሥራት ዛሬ በእግዚአብሔር ላይ እናምፅን? እርሱን ማምለካችንንም እንተውን? ይህ ከእኛ ይራቅ!”
የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም፣ የሮቤልን የጋድንና የምናሴን ወገኖች “በዚህ ነገር እግዚአብሔርን አልበደላችሁምና፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ መሆኑን ዛሬ ዐውቀናል፤ እነሆ እስራኤላውያንን ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል” አላቸው።
እስራኤላውያንም ይህን ሲሰሙ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከዚያም የሮቤልና የጋድ ወገኖች የሚኖሩበትን አገር በጦርነት ለማጥፋት የመሄድን ነገር አላነሡም።
እግዚአብሔር የምድያማውያንን መሪዎች ሔሬብንና ዜብን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣችሁ፤ ታዲያ እናንተ ከፈጸማችሁት ጋራ የሚወዳደር ምን ማድረግ እችል ነበር?” ይህን ሲሰሙ ቍጣቸው በረደ።
ስለዚህ አንኩስ ዳዊትን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ሕያው እግዚአብሔርን አንተ ታማኝ ነህ፤ ወደ እኔ እዚህ ከመጣህበት ቀን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምንም ጥፋት ያላገኘሁብህ ስለ ሆነ፣ ዐብረኸኝ ብትዘምት በበኩሌ ደስተኛ ነበርሁ፤ ነገር ግን ገዦቹ አልተቀበሉህም፤