ኢያሱ 22:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ካህኑ ፊንሐስና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝቡ የላካቸው የምዕራብ ነገዶች የቤተሰብ አለቆች የሆኑት ታላላቅ ሰዎች፥ የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ በሚኖሩ የምናሴ ነገዶች ሕዝብ የተናገሩትን ሰምተው መልሱ አረካቸው፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ካህኑ ፊንሐስና የእስራኤላውያን የጐሣ መሪዎች የነበሩት የማኅበረ ሰቡ አለቆች የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ወገኖች ያሉትን በሰሙ ጊዜ ተደሰቱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ነገድ አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃላት በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት የእስራኤል መሳፍንት ሁሉ ፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፤ ደስም አሰኛቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል አእላፋት አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው። Ver Capítulo |