ኢያሱ 21:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንፍታሌም ነገድ፣ በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞት-ዶንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንፍታሌም ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው ሦስት ከተሞች በገሊላ ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ቄዴሽ፥ ሐሞት፥ ዶርና ቃርታን ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማርያዋን፥ ኤማትንና መሰማርያዋን፥ ቃርቴንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነቸውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰምርያዋን፥ ሐሞትዶንና መሰምርያዋን፥ ቀርታንንና መሰምርያዋን፥ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። |
ስለዚህም በኰረብታማው በንፍታሌም ምድር በገሊላ ቃዴስን፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ሴኬምን፣ በኰረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት አርባቅን ለዩ።
ዲቦራ፣ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺሕ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤