ኢያሱ 21:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ በከተማዪቱ ዙሪያ ያሉትን ዕርሻዎችና መንደሮች ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኔ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ በከተማይቱ የሚገኘው የእርሻ ቦታና በክልልዋ ውስጥ ያሉት መንደሮች አስቀድሞ ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነው ተሰጥተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም የከተማዪቱን እርሻ መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ልጆች ርስት አድርጎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኔ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት። |
እነርሱም በተራራማው የይሁዳ ምድር ያለችውን ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን በዙሪያዋ ካለው መሰማሪያ ጋራ ሰጧቸው፤ አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።