መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ የመጀመሪያው ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ ከቀዓት ጐሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያዎች እነዚህ ነበሩ።
ኢያሱ 21:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም ከተሞች የሌዊ ልጆች፣ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለአሮን ዝርያዎች ተመደቡ፤ ይህም የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣላቸው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ ከሌዊ ነገድ የአሮን ዘሮች ለሆኑት ለቀዓት ወገኖች ተሰጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። |
መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ የመጀመሪያው ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ ከቀዓት ጐሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያዎች እነዚህ ነበሩ።
እነርሱም በተራራማው የይሁዳ ምድር ያለችውን ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን በዙሪያዋ ካለው መሰማሪያ ጋራ ሰጧቸው፤ አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።
የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ዘሮች በየጐሣቸው ወጣ፤ የካህኑ የአሮን ዝርያዎች ለሆኑት ሌዋውያን ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።