ኢያሱ 16:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎዛ ከምትባለው ከቤቴል ይነሣና በአጣሮት ወደሚገኘው ወደ አርካውያን ግዛት ይሻገራል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ግዛት በኩል ወደ ዓጣሮት አለፈ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቤትኤልም ተነሥቶ አርካውያን የሚኖሩበትን ዐጣሮትአዳርን በማለፍ ወደ ሎዛ ይዘልቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቤቴል ሎዛም በከሮንቲ ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አውራጃ ይደርሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አለፈ፥ |
ዳዊትም ሕዝቡ እግዚአብሔርን ወደሚያመልክበት ወደ ተራራው ጫፍ ሲደርስ፣ አርካዊው ኩሲ ልብሱን ቀድዶ ትቢያ በራሱ ላይ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ።
ምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞች፣ በስተምሥራቅ ነዓራን፣ በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን፣ እንዲሁም ሴኬምንና መንደሮቿን፣ ከዚያም ዐልፎ ጋያንና መንደሮቿን በሙሉ ያጠቃልል ነበር።
ከዚያ ደግሞ ወደ ደቡብ ሎዛ ማለት ወደ ቤቴል ተረተር ይሻገርና በታችኛው ቤትሖሮን በስተ ደቡብ ባለው ተራራ በኩል አድርጎ ወደ አጣሮት አዳር ይወርዳል።