አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ የሆነው የጊሎን ሰው አኪጦፌል ከአገሩ ከጊሎ ወደ እርሱ እንዲመጣ ላከበት፤ ስለዚህ ሤራው ጥንካሬ አገኘ፤ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቍጥር እየጨመረ መጣ።
ኢያሱ 15:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጎሶም፣ ሖሎንና ጊሎ፤ እነዚህም ዐሥራ አንዱ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፤ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጎሼን፥ ሖሎንና ጊሎ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አንድ ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትንም ትናንሽ ከተሞችን ያጠቃልላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጎሶም ከሉም፥ ከናም፥ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ የሆነው የጊሎን ሰው አኪጦፌል ከአገሩ ከጊሎ ወደ እርሱ እንዲመጣ ላከበት፤ ስለዚህ ሤራው ጥንካሬ አገኘ፤ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቍጥር እየጨመረ መጣ።
ኢያሱ ያን ምድር በሙሉ፣ ማለት ተራራማውን አገር፣ ኔጌብን ሁሉ፣ የጎሶምን ምድር በሙሉ፣ የምዕራቡን ቈላ፣ ዓረባን እንዲሁም የእስራኤልን አገር ደጋውንና ቈላውን ጠቅልሎ ያዘ፤