ኢያሱ 13:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሸለቆው ውስጥ ደግሞ ቤትሀራምን፣ ቤትኒምራን፣ ሱኮትን፣ ዳፎንንና እስከ ኪኔሬት ባሕር ጫፍ የሚደርሰውን ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ቀሪውን የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት ያካትታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የተቀረውም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዮርዳኖስ ሸለቆ በተለይ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን መንግሥት ቅሬታ የሆኑትን ቤትሐራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን ተብለው የሚጠሩትን ጭምር ያጠቃልላል፤ በምዕራብ በኩል የሚዋሰናቸውም የዮርዳኖስ ወንዝ ሲሆን፥ በሰሜን እስከ ገሊላ ባሕር ይደርሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትንምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኬኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር። |
ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጻርታን መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ።
ወሰኑም ከሴፋማ አንሥቶ ከዓይን በስተምሥራቅ እስካለው እስከ ሪብላ ቍልቍል ይወርድና ከኪኔሬት ባሕር በስተምሥራቅ እስካሉት ሸንተረሮች ድረስ ይዘልቃል።
የምዕራቡ ወሰን፣ በዓረባ የሚገኘው ዮርዳኖስ ሲሆን፣ ይኸውም ከፈስጋ ተረተሮች በታች፣ ከኪኔሬት አንሥቶ የጨው ባሕር እስከሚባለው እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ነው።
እንዲሁም ከኪኔሬት ባሕር እስከ ጨው ባሕር ያለውን ምሥራቃዊውን ዓረባ፣ እስከ ቤትየሺሞትና ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ ፈስጋ ተራራ ግርጌ ድረስ ገዝቷል።