ዮናስ 1:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በርሷ ላይ ስበክ፤ ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቷልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ተነሥ፥ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ በእርሷ ላይ ስበክ፤ ክፋታቸው በፊቴ ወጥቶአልና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክፋታቸውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥቶአልና ለእነርሱ ስበክ።” |
ዖዴድ የተባለ የእግዚአብሔር ነቢይ በዚያ ስለ ነበር፣ ሰራዊቱ ወደ ሰማርያ በተመለሰ ጊዜ ለመቀበል ወጣ፤ እንዲህም አላቸው፤ “የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ይሁዳን ስለ ተቈጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣችሁ፤ እናንተ ግን እስከ ሰማይ በሚደርስ ቍጣ ፈጃችኋቸው።
እንዲህ ስል ጸለይሁ፤ “አምላኬ ሆይ፤ ኀጢአታችን ከራሳችን በላይ ሆኗል፤ በደላችንም እስከ ሰማያት ደርሷል፤ አምላኬ ሆይ፤ ፊቴን ወደ አንተ ቀና ለማድረግ ፈራሁ፤ እጅግም ፈራሁ።
ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የርሱን ስም አላነሣም፤ በስሙም አልናገርም” ብል፣ ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም።
ዮናስም የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዘ፤ ወደ ነነዌም ሄደ። በዚህ ጊዜ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷንም ከዳር እስከ ዳር ለመጐብኘት ሦስት ቀን ያስፈልግ ነበር።
ታዲያ፣ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ፣ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሰዎችና አያሌ እንስሳት ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን አይገባኝምን?”
ቍስልህን ሊፈውስ የሚችል የለም፤ ስብራትህም ለሞት የሚያደርስ ነው። ስለ አንተ የሰማ ሁሉ፣ በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፤ ወሰን የሌለው ጭካኔህ ያልነካው ማን አለና?
የነነዌ ሰዎች በፍርድ ዕለት ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ እነርሱ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና። እነሆ፤ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።
ልብ በሉ፤ ዕርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የዐጫጆቹም ጩኸት ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው ጌታ ጆሮ ደርሷል።