La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 9:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ይህ የሆነው የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተው ስላልታዘዙኝና ሥርዐቴን ስላልተከተሉ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ድምፄንም አልሰሙምና፥ በእርሱም አልተመላለሱምና፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ሕዝቤ እኔ የሰጠኋቸውን ሕግ በመተዋቸው ነው፤ እነርሱ ለእኔ አልታዘዙም፤ የነገርኳቸውንም ሁሉ አልፈጸሙም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ሕዝቤ በፊ​ታ​ቸው የሰ​ጠ​ኋ​ቸ​ውን ሕጌን ትተ​ዋል፤ ቃሌ​ንም አል​ሰ​ሙም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ቃሌንም አልሰሙምና፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 9:13
11 Referencias Cruzadas  

“እናንተ ግን እኔን ከመከተል ተመልሳችሁ የሰጠኋችሁን ሥርዐቶቼንና ትእዛዞቼን ብትተዉ፣ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታገለግሉና ብታመልኳቸው፣


“አሁን ግን አምላካችን ሆይ፤ ከዚህ በኋላ ምን እንላለን? ትእዛዞችህን አቃልለናልና፤


ሕግህን ከተዉ ክፉዎች የተነሣ፣ ቍጣ ወረረኝ።


ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።


ቃሌን መስማት እንቢ ብለው በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ ሊያመልኳቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን ጣዖቶች የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝቦች ከጥቅም ውጭ እንደ ሆነው እንደዚህ መቀነት ይበላሻሉ።


ከዚያም፣ ‘የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ኪዳን ትተው ሌሎችን አማልክት ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው’ ይላሉ።”


ሕዝቡ፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ይህን ሁሉ ነገር ለምን አደረገብን?’ ብለው ቢጠይቁ፣ ‘እኔን፣ እንደ ተዋችሁኝና በራሳችሁ ምድር ባዕዳን አማልክትን እንዳገለገላችሁ፣ እንደዚሁ የእናንተ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።


ሕዝቡ ግን አልሰማኝም፤ ልብ ብሎ ለማድመጥም አልፈለገም፤ ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ አባቶቻቸው ከሠሩት የባሰም ክፉ አደረጉ።’