ከአባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በደላችን ታላቅ ነው። ከኀጢአታችንም የተነሣ፣ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ እኛም ሆንን፣ ነገሥታቶቻችንና ካህናቶቻችን በባዕዳን ነገሥታት እጅ ወድቀን ለሰይፍ፣ ለምርኮ፣ ለብዝበዛና ለውርደት ተዳርገናል።
ኤርምያስ 7:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ይህን የሚያደርጉት እኔን ለማስቈጣት ነውን? ይላል እግዚአብሔር፤ ይልቁን ይህን በማድረጋቸው በሚደርስባቸው ዕፍረት የሚጐዱት ራሳቸውን አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔን ያስቈጣሉን? ይላል ጌታ፤ ለፊታቸውስ እፍረት አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ እኔን የሚያስቈጡ ይመስላቸዋልን? ይልቅስ ራሳቸውን ይጐዳሉ፤ ኀፍረትንም በራሳቸው ላይ ያመጣሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔን ያስቈጣሉን? ይላል እግዚአብሔር፤ ፊታቸው ያፍር ዘንድ ለራሳቸው አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔን ያስቈጣሉን? ይላል እግዚአብሔር፥ ለፊታቸውስ እፍረት አይደለምን? |
ከአባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በደላችን ታላቅ ነው። ከኀጢአታችንም የተነሣ፣ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ እኛም ሆንን፣ ነገሥታቶቻችንና ካህናቶቻችን በባዕዳን ነገሥታት እጅ ወድቀን ለሰይፍ፣ ለምርኮ፣ ለብዝበዛና ለውርደት ተዳርገናል።
ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤ “ወዮ! በባላንጣዎቼ ላይ ቍጣዬን እገልጣለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።
የሰባቶቹ እናት ትዝለፈለፋለች፤ ትንፋሿም ይጠፋል፤ ገና ቀን ሳለ ፀሓይዋ ትጠልቃለች፤ እርሷም ታፍራለች፤ ትዋረዳለችም፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት፣ ለሰይፍ እዳርጋቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።
ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤ ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤ እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣ እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣ ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋራ ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም።
እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን፤ እኛም አባቶቻችንም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።”
ይህም የሆነው ስላደረጉት ክፋት ነው። እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ ላላወቋቸው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ አስቈጥተውኛል።
እንዲህ የሚለውን የሕዝቤን ጩኸት፣ ከሩቅ ምድር ስማ፤ “እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ንጉሧስ በዚያ አይኖርምን?” “በተቀረጹ ምስሎቻቸው፣ እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ለምን አስቈጡኝ?”
እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቷል፤ እንዲህም ይላል፤ ‘ምንኛ ወደቅን! ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው! ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤ አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”