ኤርምያስ 52:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛው ወር በዘጠነኛው ቀን በከተማዪቱ ራብ ጸንቶ ስለ ነበር ሕዝቡ የሚበላውን ዐጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛውም ወር በዘጠነኛው ቀን በከተማይቱ ራብ ጸንቶ ነበር፥ ለአገሬውም ሰው እንጀራ ታጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያው ዓመት በአራተኛው ወር፥ በዘጠነኛው ቀን፥ ሕዝቡ የሚመገቡት አጥተው ራብ ጸና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛውም ወር በዘጠነኛው ቀን በከተማዪቱ ራብ ጸንቶ ነበር፤ ለሀገሩም ሰዎች እንጀራ ታጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ወር በዘጠነኛው ቀን በከተማይቱ ራብ ጸንቶ ነበር፥ ለአገሩም ሰዎች እንጀራ ታጣ። |
እነርሱም፣ ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ለሞት የተመደበ ወደ ሞት፣ ለሰይፍ የተመደበ ወደ ሰይፍ፣ ለራብ የተመደበ ወደ ራብ፣ ለምርኮ የተመደበ ወደ ምርኮ ይሄዳል።’
የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚሹ ጠላቶቻቸው ከብበው ሲያስጨንቋቸው፣ አንዱ የሌላውን ሥጋ ይበላል።’
በዚህች ከተማ የሚቈይ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በመቅሠፍት ይሞታል፤ ወጥቶ ለከበቧችሁ ባቢሎናውያን እጁን የሚሰጥ ግን ነፍሱን ያተርፋል፤ በሕይወትም ይኖራል።
ንጉሡም ሴዴቅያስ፣ ኤርምያስ በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ እንዲቀመጥና በከተማዪቱ ያለው እንጀራ እስኪያልቅ ድረስ ከእንጀራ ጋጋሪዎች ሰፈር በየቀኑ አንድ አንድ እንጀራ እንዲሰጠው አዘዘ፤ ስለዚህ ኤርምያስ በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ ተቀመጠ።
“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እነዚህ ሰዎች በነቢዩ በኤርምያስ ላይ ባደረጉት ነገር ሁሉ ክፋትን አድርገዋል፤ ከከተማዪቱም እንጀራ በጠፋ ጊዜ በራብ እንዲሞት ጕድጓድ ውስጥ ጥለውታል።”
እንጀራ በመፈለግ፣ ሕዝቧ ሁሉ በሥቃይ ይጮኻል፤ በሕይወት ለመኖር፣ የከበረ ሀብታቸውን በምግብ ይለውጣሉ፤ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ ተመልከተኝም፤ እኔ ተዋርጃለሁና።”
“የሰው ልጅ ሆይ፤ አንድ አገር በእኔ ባለ መታመን ቢበድለኝና እኔም እጄን በላዩ ዘርግቼ የምግብ ምንጩን ባደርቅ፣ ራብንም አምጥቼበት ሰውንና እንስሳቱን ብገድል፣
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ሰውንና እንስሳቱን ለማጥፋት አራቱን አስፈሪ ፍርዶቼን፦ ሰይፍን፣ ራብን፣ የዱር አራዊትንና ቸነፈርን በኢየሩሳሌም ላይ በማመጣበት ጊዜ ምንኛ የከፋ ይሆን!
የሚገድለውንና አጥፊ የሆነውን የራብ ፍላጻ በእናንተ ላይ በምወረውርበት ጊዜ በርግጥ ላጠፋችሁ እሰድዳለሁ። በራብ ላይ ራብ አመጣባችኋለሁ፤ የምግብ ምንጫችሁንም አደርቃለሁ።
የእንጀራችሁ እህል እንዲቋረጥ በማደርግበት ጊዜ፣ ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ላይ እንጀራ ይጋግራሉ፤ እንጀራውንም በሚዛን መዝነው እናንተም ትበላላችሁ፤ ግን አትጠግቡም።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአራተኛው፣ የአምስተኛው፣ የሰባተኛውና የዐሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”
የሚያጠፋ ራብ፣ በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድድባቸዋለሁ፤ የአራዊትን ሹል ጥርስ፣ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድድባቸዋለሁ።