ኤርምያስ 51:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስተኛው ቀስቱን እስኪገትር፣ የጦር ልብሱንም እስኪለብስ ፋታ አትስጡት፤ ለወጣቶቿ አትዘኑ፤ ሰራዊቷንም ፈጽማችሁ አጥፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስተኛው ቀስቱን አይገትር ጥሩሩንም ለብሶ አይነሣ፤ ለጐልማሶችዋ አትዘኑ ሠራዊትዋንም ሁሉ አጥፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮችዋ ቀስታቸውን እስኪገትሩና ወይም የጦር ልብሳቸውን እስኪለብሱ ጊዜ አትስጡአቸው፤ ለወጣቶችዋ በመራራት ምሕረት አታድርጉ፤ ሠራዊትዋን በሙሉ ደምስሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀስት ወርዋሪው ላይ፥ በጥሩርም በሚነሣው ላይ ቀስተኛው ቀስቱን ይገትር፤ ለጐበዛዝቷ አትዘኑ፤ ሠራዊቷንም ሁሉ አጥፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወርዋሪው ላይ በጥሩርም በሚነሣው ላይ ቀስተኛው ቀስቱን ይገትር፥ ለጐበዛዝትዋ አትዘኑ ሠራዊትዋንም ሁሉ አጥፉ። |
“የምራታይምን ምድር፣ የፋቁድ ነዋሪዎችንም፣ አሳድዷቸው፤ ግደሏቸው፤ ፈጽማችሁም አጥፏቸው፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “ያዘዝኋችሁንም ሁሉ አድርጉ።