ኤርምያስ 48:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መዳፉን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ከንቱ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር። “ጕራውም ፋይዳ አይኖረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ እብሪቱን አውቃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ፉከራው ሐሰት ነው፥ ሥራውም ሐሰት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የእርስዋን ዕብሪተኛነት ዐውቃለሁ፤ ፉከራዋና ሥራዋ ከንቱ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ሥራውን አውቃለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ እንደ ኀይሉም መጠን እንዲሁ ያደረገ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጣው ምንም እንደ ሆነ አውቃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፉከራው ምንም አልሠራም። |