ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
ኤርምያስ 48:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣ የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መፍረስና ታላቅ ጥፋት፥ የሚል የጩኸት ድምፅ ከሖሮናይም ተሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሖሮናይም ላይ በሚደርሰው ውድመትና ጥፋት የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መፍረስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መፍረስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ። |
ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤ እንባቸውን እያፈሰሱ ወደ ሉሒት ወጡ፤ በሖሮናይም መንገድም፣ ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፤ ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤ አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣ ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል። ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤
“ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤ የኔምሬም ውሃ እንኳ ደርቋልና።