ኤርምያስ 48:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤ የሞዓብን መደምሰስ፣ በአርኖን አጠገብ አስታውቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሞዓብም ፈርሶአልና አፈረ፤ አልቅሱ ጩኹም፤ ሞዓብ እንደ ጠፋ በአርኖን አጠገብ አውጁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብ ፈራርሳ በዕፍረት ስለ ወደቀች ዋይ ዋይ ብላችሁ አልቅሱላት፤ ባድማ መሆንዋንም በአርኖን ወንዝ አጠገብ ተናገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሞአብ ፈርሳለችና አፈረች፤ አልቅሱ፥ ጩኹም፤ ሞአብ እንደ ጠፋች በአርኖን አውሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሞዓብም ፈርሶአልና አፈረ፥ አልቅሱ ጩኹም፥ ሞዓብ እንደ ተዘረፈ በአርኖን አጠገብ አውሩ። |
በአርኖን ሸለቆ ጫፍ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆው ውስጥ ከምትገኘዋ ከተማ አንሥቶ እስከ ገለዓድ ካሉት ከተሞች አንዳቸውም እንኳ ሊገቱን አልቻሉም። አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን።
ይህም ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔርና በሸለቆው መካከል ካለችው ከተማ አንሥቶ እስከ ዲቦን የሚደርሰውን የሜድባን ደጋማ ምድር በሙሉ ይይዛል፤
“ቀጥሎም የኤዶምንና የሞዓብን ምድር በመዞር፣ በምድረ በዳው ተጕዞ ከሞዓብ በስተምሥራቅ በኩል በማለፍ ከአርኖን ማዶ ሰፈረ፤ የሞዓብም ድንበር አርኖን ስለ ነበር ወደ ሞዓብ ክልል አልገባም።