ኤርምያስ 43:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና፣ የጦር መኰንኖቹ ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ በሙሉ እግዚአብሔር በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን ቃል አልሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ የጌታን ድምፅ አልሰሙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ዮሐናንም ሆነ የሠራዊት አለቆች ሁሉ፥ እንዲሁም ከሕዝቡ ወገን ማንም በይሁዳ ምድር ለመኖር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልፈጸሙም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የጭፍራ አለቆችም ሁሉ፥ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይቀመጡ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይቀመጡ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም። |
እርሱም በመናገር ላይ ሳለ፣ ንጉሡ፣ “ለመሆኑ አንተን የንጉሥ አማካሪ አድርገን ሾመንሃልን? ዝም አትልም እንዴ! መሞት ትፈልጋለህ?” አለው። ነቢዩም ዝም አለ፤ ሆኖም፣ “ይህን አድርገሃልና ምክሬንም አልሰማህምና፤ አምላክ ሊያጠፋህ እንደ ወሰነ ዐውቃለሁ” አለ።
የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ከርሱ ጋራ የነበሩት የጦር መኰንኖች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ፣ በምጽጳ ከማረካቸው የተረፉትን ሰዎች በማስመለስ ይዘው ሄዱ፤ እነዚህም፣ ወታደሮች፣ ሴቶች ሕፃናትና ከገባዖን ያመጧቸው የቤተ መንግሥት ባለሥልጣኖች ነበሩ።