ነገር ግን በሰባተኛው ወር ንጉሣዊ ዝርያ የነበረው የኤሊሳማ የልጅ ልጅ የሆነው የናታንያ ልጅ እስማኤል ዐሥር ሰዎች ይዞ መጥቶ ጎዶልያስንና በምጽጳ ዐብረውት የነበሩትን የይሁዳን ሰዎችና ባቢሎናውያንን ገደለ።
ኤርምያስ 41:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እስማኤል በምጽጳ ከጎዶልያስ ጋራ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፣ በዚያም የተገኙትን የባቢሎን ወታደሮች ገደላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፥ በዚያም የተገኙትን የከለዳውያንን ወታደሮች ሁሉ ገደላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስማኤል በምጽጳ ከገዳልያ ጋር የነበሩትን አይሁድንና በዚያ ተገኝተው የነበሩትን የባቢሎናውያንን ወታደሮች ጭምር ፈጀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር በመሴፋ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፥ በዚያም የተገኙትን ከለዳውያንን ሁሉ፤ ሰልፈኞች ሰዎችንም ሁሉ ገደላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፥ በዚያም የተገኙትን የከለዳውያንን ሰልፈኞች ሁሉ ገደላቸው። |
ነገር ግን በሰባተኛው ወር ንጉሣዊ ዝርያ የነበረው የኤሊሳማ የልጅ ልጅ የሆነው የናታንያ ልጅ እስማኤል ዐሥር ሰዎች ይዞ መጥቶ ጎዶልያስንና በምጽጳ ዐብረውት የነበሩትን የይሁዳን ሰዎችና ባቢሎናውያንን ገደለ።
የናታንያ ልጅ እስማኤልና ዐብረውት የነበሩ ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው፣ የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ ገዥ አድርጎ የሾመውን የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱት፤ ገደሉትም።
በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጕንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣ የሚያጽናናት ማንም የለም፤ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላቶቿም ሆነዋል።