ኤርምያስ 22:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣ አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤ በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣ መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህ ሰው ልጆቹን ሁሉ አጥቶ ኑሮው የማይሳካለት እንዲሆን ተፈርዶበታል፤ የዳዊትን ዙፋን ለመውረስ በይሁዳ የሚነግሡ ዘሮች አይተርፉለትም ብለሽ መዝግቢ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዘመኑ አይከናወንምና፥ ከዘሩም በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ አይነሣምና፥ እንግዲህ ወዲህም ለይሁዳ ገዢ አይሾምምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠሪው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ኔሔላማዊውን ሸማያንና ዘሩን እቀጣለሁ፤ በእኔ ላይ ዐመፅን ተናግሯልና፣ በዚህ ሕዝብ መካከል የሚተርፍ ዘር አይኖረውም” ይላል እግዚአብሔር፤ ለሕዝቤ የማደርገውንም መልካም ነገር አያይም።’ ”
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከዘሩ አይገኝም፤ ሬሳውም ወደ ውጭ ተጥሎ ለቀን ሐሩርና ለሌሊት ቍር ይጋለጣል።