ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።
ኤርምያስ 22:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እረኞችሽ ሁሉ በነፋስ ይወሰዳሉ፤ ወዳጆችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ ከክፋትሽም ሁሉ የተነሣ፣ ታፍሪያለሽ፤ ትዋረጂያለሽም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እረኞችሽን ሁሉ ንፋስ ያሰማራቸዋል፥ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ በዚያን ጊዜም ስለ ኃጢአትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትዋረጃለሽም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትሠሩት ኃጢአት ምክንያት ነፋስ ገለባን ጠራርጎ እንደሚወስድ፥ መሪዎቻችሁ ተጠራርገው ይወሰዳሉ። የተማመናችሁባቸው የጦር ጓደኞቻችሁም ተማርከው ወደ ባዕድ ሀገር ይወሰዳሉ፤ ኀፍረትና ውርደትም ይደርስባችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይወስዳቸዋል፤ ወዳጆችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ፤ በወዳጆችሽም ፊት ቷረጃለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፥ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፥ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትጐሳቈይማለሽ። |
ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ባሮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ ባሮቼ ይጠጣሉ፤ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ ባሮቼ ደስ ይላቸዋል፤ እናንተ ግን ታፍራላችሁ።
‘እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው ካህናቱ አልጠየቁም፤ ከሕጉ ጋራ የሚውሉት አላወቁኝም፤ መሪዎቹ ዐመፁብኝ፤ ነቢያቱም በበኣል ስም ተነበዩ፤ ከንቱ ነገሮችን ተከተሉ።
ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋራ ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም።
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተም ግድ የላቸውም። ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤ እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤ በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ነውና።
አንቺ ለጥፋት የተዳረግሽ ሆይ፤ ምን መሆንሽ ነው? ቀይ ቀሚስ የለበስሽው ለምንድን ነው? ለምን በወርቅ አጌጥሽ? ዐይኖችሽንስ ለምን ተኳልሽ? እንዲያው በከንቱ ተሽሞንሙነሻል፤ የተወዳጀሻቸው ንቀውሻልና፤ ነፍስሽንም ሊያጠፉ ይፈልጋሉ።
ለመሆኑ ይህን የሚያደርጉት እኔን ለማስቈጣት ነውን? ይላል እግዚአብሔር፤ ይልቁን ይህን በማድረጋቸው በሚደርስባቸው ዕፍረት የሚጐዱት ራሳቸውን አይደለምን?
ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋራ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብጽ ይልካል።
በወንድሞቹ መካከል ቢበለጽግም እንኳ፣ የምሥራቅ ነፋስ ከምድረ በዳ እየነፈሰ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል፤ ምንጩ ይነጥፋል፤ የውሃ ጕድጓዱም ይደርቃል። የከበረው ሀብቱ ሁሉ፣ ከግምጃ ቤቱ ይበዘበዛል።