ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።
ኤርምያስ 22:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ባለትልልቅ ሰገነት፣ ሰፊ ቤተ መንግሥት ለራሴ እሠራለሁ’ ለሚል ወዮለት! ሰፋፊ መስኮቶችን ያበጅለታል፤ በዝግባ ዕንጨት ያስጌጠዋል፤ ቀይ ቀለምም ይቀባዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ’ ለሚል፥ መስኮቶችንም ለሚያወጣለት፥ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጠው፥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሰው “ለራሴ ትልቅ ቤት ከሰፊ ሰገነት ጋር እሠራለሁ፤ እንዲሁም ሰፋፊ መስኮቶችን አወጣለታለሁ፤ ቤቱን በሰፋፊ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት አስጌጠዋለሁ፤ ደማቅ ቀይ ቀለምም እቀባዋለሁ” ይላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለራሴ ሰፊ ቤት፥ ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፥ መስኮትንም ለሚያወጣ፥ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጥ፥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፥ መስኮትንም ለሚያወጣ፥ በዝግባም ሥራ ለሚያሳጌጥ፥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት! |
ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።
ጌታ እግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሏል፤ ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
ኤዶምያስ፣ “ብንደመሰስም እንኳ የፈረሰውን መልሰን እንሠራዋለን” ይል ይሆናል። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ “እነርሱ ይሠሩ ይሆናል፤ እኔ ግን አፈርስባቸዋለሁ፤ ክፉ ምድር፣ እግዚአብሔርም ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ተብለው ይጠራሉ።