ኤርምያስ 21:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በተጨማሪም ለዚህ ሕዝብ እንዲህ በል፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አድርጌአለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለዚህም ሕዝብ እንዲህ በል፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በፊታችሁ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ አኑሬአለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ፦ “እነሆ አድምጡ! እኔ እግዚአብሔር ወደ ሕይወት የሚወስደውንና ወደ ሞት የሚያደርሰውን መንገድ በፊታችሁ አኑሬአለሁ፤ ከሁለቱ አንዱን ምረጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዚህም ሕዝብ እንዲህ በል፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በፊታችሁ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ አድርጌአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዚህም ሕዝብ እንዲህ በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በፊታችሁ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ አድርጌአለሁ። |
ኤርምያስም ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ብትሰጥ፣ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ አትቃጠልም፤ አንተና ቤተ ሰብህም በሕይወት ትኖራላችሁ።
ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤