ኤርምያስ 18:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊይዙኝ ጕድጓድ ስለ ቈፈሩ፣ ለእግሮቼም በስውር ወጥመድ ስለ ዘረጉ፣ በድንገት ወራሪ ስታመጣባቸው፣ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊይዙኝ ጉድጓድ ቆፍረዋልና፥ ለእግሮቼም ወጥመድ ሸሽገዋልና ድንገት በላያቸው ጭፍራ ባመጣህ ጊዜ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወራሪዎችን በድንገት ላክባቸው፤ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ እነርሱ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቆፍረዋል፤ የምያዝበትንም ወጥመድ አዘጋጅተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊይዙኝ ጕድጓድ ቈፍረዋልና፥ ለእግሮችም ወጥመድ ሸሽገዋልና፥ በቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ ድንገትም በላያቸው ወንበዴን አምጣባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊይዙኝ ጕድጓድ ቆፍረዋልና፥ ለእግሮቼም ወጥመድ ሸሽገዋልና ድንገት በላያቸው ጭፍራ ባመጣህ ጊዜ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ። |
የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን? እነርሱ ግን ጕድጓድ ቈፈሩልኝ፤ ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣ በፊትህ ቆሜ፣ ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ ዐስብ።
“በየቦታው ሽብር አለ፤ አውግዙት፤ እናውግዘው፤” ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤ መውደቄን በመጠባበቅ፣ ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣ “ይታለል ይሆናል፣ ከዚያም እናሸንፈዋለን፤ እንበቀለዋለንም” ይላሉ።
የበኵር ልጇን ለመውለድ እንደምታምጥ፣ በወሊድ እንደምትጨነቅ ሴት ድምፅ ሰማሁ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ትንፋሽ ዐጥሯት ስትጮኽ፣ እጇን ዘርግታ፣ “ወዮልኝ! ተዝለፈለፍሁ፣ በነፍሰ ገዳዮች እጅ ወደቅሁ!” ስትል ሰማሁ።
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ ምርር ብለሽ አልቅሺ፤ አጥፊው በድንገት፣ በላያችን ይመጣልና።