ኤርምያስ 15:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰው ብረትን፣ ከሰሜን የመጣን ብረት፣ ንሓስንስ መስበር ይችላልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ከነሐስ ጋር የተቀላቀለን ብረት ለመስበር እንደማትችሉ ሁሉ በሰሜን በኩል ከጠላት የተቃጣውን አደጋ ልታሸንፉ አትችሉም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? |
“ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ ከሠሪው ጋራ ክርክር ለሚገጥም ወዮለት! ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣ ‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን? የምትሠራውስ ሥራ፣ ‘እጅ የለህም’ ይልሃልን?
የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እንዲያገለግሉ፣ በእነዚህ ሕዝቦች ላይ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ፤ እነርሱም ይገዙለታል፤ በዱር አራዊት ላይ እንኳ ሥልጣን እሰጠዋለሁ።’ ”