ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤ ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤ ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣ የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤
ኤርምያስ 14:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሜዳ አህዮች ባድማ ኰረብቶች ላይ ቆሙ፤ እንደ ቀበሮም አየር ፍለጋ አለከለኩ፤ ግጦሽ ባለመገኘቱ፣ ዐይኖቻቸው ፈዘዙ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሜዳ አህዮችም በተራቈቱ ኮረብቶች ላይ ቆመዋል፥ እንደ ቀበሮም ወደ ነፋስ አለከለኩ፤ ልምላሜም የለምና ዐይኖቻቸው ጠወለጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሜዳ አህዮች ከውሃ ጥም የተነሣ፥ በየኰረብታው ጫፍ ላይ ቆመው እንደ ቀበሮ ያለከልካሉ፤ ምግብ ስለማያገኙም የማየት ኀይላቸው ይቀንሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመዋል፤ እንደ ሰገኖም ወደ ነፋስ አለከለኩ፤ ሣርም የለምና ዐይኖቻቸው ጠወለጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመዋል፥ እንደ ቀበሮም ወደ ነፋስ አለከለኩ፥ ልምላሜም የለምና ዓይኖቻቸው ጠወለጉ። |
ዐምባ ምሽጉ ወና ይሆናል፤ ውካታ የበዛበት ከተማ ጭር ይላል፤ ምሽጉና ማማው ለዘላለሙ ዋሻ፣ የዱር አህያ መፈንጫ፣ የመንጋም መሰማሪያ ይሆናል፤
በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣ በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤ ከመጐምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል? ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች።