በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ ሳለ፣ ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ።
ኤርምያስ 12:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከእግረኞች ጋራ ሮጠህ፣ እነርሱ ካደከሙህ፣ ከፈረሰኞች ጋራ እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ? በሰላም አገር ከተሰናከልህ፣ በዮርዳኖስ ደን ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ተሰናክለህ ከወደቅህ፥ በዮርዳኖስ ዱር እንዴት ታደርጋለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! በእግር ሩጫ ከሰዎች ጋር መወዳደር የሚያደክምህ ከሆነ፥ ከፈረስ ጋር መወዳደር እንዴት ትችላለህ? ግልጥ በሆነው ሜዳ ላይ ጸንተህ መቆም ካቃተህ፥ በዮርዳኖስ ደን ውስጥ መቆም እንዴት ትችላለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግሮችህ ሮጠው ይደክማሉ፤ ፈረሶችን ለምን ታስጌጣለህ? በሰላምም ምድር ላይ ለምን ትታመናለህ? በዮርዳኖስስ ጩኸት ለምን እንዲህ ታደርጋለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ታምነህ ብትቀመጥ፥ በዮርዳኖስ ትዕቢት እንዴት ታደርጋለህ? |
በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ ሳለ፣ ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ።
“እንግዲህ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹና፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር፤ አለዚያ በእጃችን ትሞታለህ’ ለሚሉህ ለዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
ነገር ግን ኤርምያስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሁሉ እንዲናገር ያዘዘውን ሁሉ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፣ ካህናቱ፣ ነቢያቱና ሕዝቡም ሁሉ ይዘውት እንዲህ አሉ፤ “አንተ መገደል አለብህ!
ይልቁንም ጸሓፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይዘው ያስሩ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልን፣ የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያንና የአብድኤልን ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፤ እግዚአብሔር ግን ሰውሯቸው ነበር።
“አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች፣ ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣ እኔም በኤዶም ላይ ድንገት እወጣለሁ፤ ከምድሩም አባርረዋለሁ። የመረጥሁትን በርሱ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል? የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?”
አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች ድንገት ወጥቶ፣ ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣ እኔም ባቢሎንን ሳይታሰብ ከምድሯ አባርራታለሁ፤ የመረጥሁትንም በርሷ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል? የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?”
ወቅቱም የመከር ጊዜ በመሆኑ፣ የዮርዳኖስ ወንዝ ሞልቶ ነበር፤ ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ እግራቸው ውሃውን እንደ ነካ፣