Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 12:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! በእግር ሩጫ ከሰዎች ጋር መወዳደር የሚያደክምህ ከሆነ፥ ከፈረስ ጋር መወዳደር እንዴት ትችላለህ? ግልጥ በሆነው ሜዳ ላይ ጸንተህ መቆም ካቃተህ፥ በዮርዳኖስ ደን ውስጥ መቆም እንዴት ትችላለህ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ከእግረኞች ጋራ ሮጠህ፣ እነርሱ ካደከሙህ፣ ከፈረሰኞች ጋራ እንዴት ልትወዳደር ትችላለህ? በሰላም አገር ከተሰናከልህ፣ በዮርዳኖስ ደን ውስጥ እንዴት ልትሆን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ተሰናክለህ ከወደቅህ፥ በዮርዳኖስ ዱር እንዴት ታደርጋለህ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ሮ​ችህ ሮጠው ይደ​ክ​ማሉ፤ ፈረ​ሶ​ችን ለምን ታስ​ጌ​ጣ​ለህ? በሰ​ላ​ምም ምድር ላይ ለምን ትታ​መ​ና​ለህ? በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስስ ጩኸት ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ታምነህ ብትቀመጥ፥ በዮርዳኖስ ትዕቢት እንዴት ታደርጋለህ?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 12:5
14 Referencias Cruzadas  

ወዳጆች ሆይ! እንደ እሳት በሚፈትን መከራ ውስጥ ስትገኙ ያልተለመደ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ አድርጋችሁ አትደነቁ፤


መከራ በሚደርስብህ ጊዜ መጽናት የማትችል ከሆንክ ምንም ብርታት የለህም ማለት ነው።


“በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ከሚገኘው ጥቅጥቅ ካለ ደን ወደ ለምለም መስክ እንደሚወጣ አንበሳ፥ እኔ እግዚአብሔር መጥቼ ባቢሎናውያን ድንገት ከከተማቸው ወጥተው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ እኔ የምመርጠውን እሾማለሁ፤ ታዲያ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ሊጠይቀኝ የሚደፍር ማነው? የሚቋቋመኝስ መሪ ማን ነው?


አንበሳ ጥቅጥቅ ካለው ከዮርዳኖስ ጫካ ወጥቶ ለምለም ወደ ሆነው ወደ በጎች መሰማርያ መስክ እንደሚመጣ እኔም በድንገት መጥቼ የኤዶም መሪዎችን አባርራለሁ፤ ከዚህ በኋላ የምመርጠውን እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ሊጠይቀኝ የሚደፍር ማን ነው? በፊቴ ቆሞ የሚቋቋመኝስ መሪ ማን ነው?


በፏፏቴህ ድምፅ ጥልቁ ጥልቁን ይጠራል፤ ማዕበልህና ሞገድህ በእኔ ላይ አለፈ።


ልጄ ሆይ! የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤ በሚገሥጽህም ጊዜ አትመረር።


የዮርዳኖስ ወንዝ በመከር ጊዜ ጐርፍ ያለው ቢሆንም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ደርሰው እግሮቻቸው የውሃውን ዳር እንደ ነኩ፥


ከዚህ በኋላ ልዑሉን ይረሕምኤልን ከዐዝርኤል ልጅ ሠራያና ከዐብድኤል ልጅ ከሸሌምያ ጋር ሆኖ እኔንና ባሮክን እንዲይዝ አዘዘው፤ እኛ ግን እግዚአብሔር ሰወረን።


እግዚአብሔር እንድናገር ያዘዘኝን ሁሉ ተናግሬ እንደ ጨረስኩ በድንገት ያዙኝና “ሞት ይገባሃል!” ሲሉ ጮኹ፥


እነዚህም የጋድ ነገድ አባሎች በአንድ ወቅት የዓመቱ የመጀመሪያ ወር እንደ ገባ፥ የዮርዳኖስም ወንዝ ከአፍ እስከ ገደፍ ሞልቶ ሳለ ወንዙን ተሻገሩ፤ ከወንዙ በሰተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ በሸለቆዎቹ ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አባረሩ።


“በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገርክ እንደ ሆነ እንገድልሃለን” ብለው የኤርምያስን ሕይወት ለማጥፋት ስለሚፈልጉት ስለ አናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios