ዘፍጥረት 48:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለያዕቆብ፣ “ልጅህ ዮሴፍ ወደ አንተ መጥቷል” ተብሎ በተነገረው ጊዜ፣ እስራኤል ተበረታትቶ ዐልጋው ላይ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለያዕቆብም፦ “እነሆ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል” ብለው ነገሩት፥ እስራኤልም ሰውነቱን አበረታቶ፥ በአልጋው ላይ ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ልጁ ዮሴፍ ሊጐበኘው መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሰውነቱን አበረታቶ በመኝታው ላይ ተቀመጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለያዕቆብም፥ “እነሆ፥ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል” ብለው ነገሩት፤ እስራኤልም ተጠነካከረ፤ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለያዕቆብም፦ እነሆ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል ብለው ነገሩች እስራኤልም ተጠነካከረ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ። |
እንዲሁም መልካሚቱ የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደ ነበረችና ንጉሡም ምን እንዳለኝ ነገርኋቸው። እነርሱም፣ “እንደ ገና መሥራቱን እንጀምር!” ካሉ በኋላ ይህን መልካም ሥራ ጀመሩ።