ዘፍጥረት 47:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን፣ “ለመሆኑ ዕድሜህ ምን ያህል ነው?” ሲል ያዕቆብን ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ያዕቆብን፦ “የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈርዖንም “ዕድሜህ ስንት ነው?” በማለት ያዕቆብን ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ያዕቆብን፥ “የኖርኸው ዘመን ስንት ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ያዕቆብን፦ የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው? አለው |
ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋራ ሲነጻጸር ዐጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት።