ዘፍጥረት 47:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን የዮሴፍን ወንድሞች፣ “ሥራችሁ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ፈርዖንን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት አርቢዎች ነን” አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ወንድሞቹን፦ “ሥራችሁ ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፦ “እኛ አገልጋዮችህ፥ እኝም አባቶቻችንም፥ በግ አርቢዎች ነን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈርዖንም የዮሴፍን ወንድሞች፦ “የምትተዳደሩበት ሥራ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት፥ “እኛ አገልጋዮችህ በግ አርቢዎች ነን፤ አባቶቻቸንም ይተዳደሩበት የነበረ ሥራ ይኸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም የዮሴፍን ወንድሞች፥ “ሥራችሁ ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፥ “እኛ አገልጋዮችህ፥ አባታችንም ከብት ጠባቂዎች ነን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ወንድሞቹም፦ ሥራችሁ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፦ እኛ ባሪያዎችን እኝም አባቶቻችንም በግ አርቢዎች ነን አሉት። |
ከዚያም፣ “ይህ ሁሉ አስጨናቂ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ንገረን፤ ሥራህ ምንድን ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?” አሉት።