ዘፍጥረት 38:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን፣ እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እጁን በመለሰው ጊዜ ወንድሙ ቀድሞት ተወለደ፤ አዋላጂቱም ሴት “እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ስለዚህ የመጀመሪያው ልጅ ስም “ፋሬስ” ተባለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ እጁን በመለሰ ጊዜ እነሆ፥ ወንድሙ ወጣ፤ እርስዋም፥ “ለምን ጥሰህ ወጣህ? ስትል ስሙን ፋሬስ” ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ እጁን በመለሰ ጊዜ እነሆ ወንድሙ ወጣ፤ እርስዋም፦ ለምን ጥስህ ወጣህ? አለች፤ |
የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስ ልጆች፦ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው።
ከይሁዳና ከብንያም ወገን የሆኑት የተቀሩት ሰዎች ደግሞ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከይሁዳ ዘሮች፦ ከፋሬስ ዘር የመላልኤል ልጅ፣ የሰፋጥያስ ልጅ፣ የአማርያ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የዖዝያ ልጅ አታያ፤
የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤