ወንዙን አሻግሮ ከሸኛቸው በኋላ፣ ጓዙን ሁሉ ሰደደ።
እነርሱን ወስዶ ወንዙን አሻገራቸው፥ ያለውን ሁሉ እንደዚሁ አሻገረ።
እነርሱን ካሻገረም በኋላ ያለውን ጓዝ ሁሉ አሻገረ።
ወሰዳቸውም፤ ወንዙንም አሻገራቸው፤ ገንዘቡንም ሁሉ አሻገረ።
ወሰዳቸውም ወንዙንም አሻገራቸው ከብቱን ሁሉ አሻገረ።
በዚያች ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ፤ ሁለቱን ሚስቶቹን እንዲሁም ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና ዐሥራ አንድ ልጆቹን ይዞ በያቦቅ መልካ ተሻገረ።
ያዕቆብ ግን ብቻውን እዚያው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስኪነጋ ድረስ ሲታገለው ዐደረ።