ዘፍጥረት 27:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመሞቴ በፊት እንድመርቅህ የምወድደውን ዐይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ አብላኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሠርተህ አምጣልኝ፤ ከበላሁም በኋላ ከመሞቴ በፊት የመጨረሻ ምርቃቴን እሰጥሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ እኔ እንደምወደው መብል አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅትህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ። |
ከዚያም፣ “በል እንግዲህ ልጄ፤ እንድመርቅህ፣ ዐድነህ ካመጣኸው አቅርብልኝና ልብላ” አለው። ያዕቆብም ምግቡን ለአባቱ አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም አመጣለት፤ እርሱም በላ፤ ጠጣም።
ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው፤ ይሥሐቅ የያዕቆብን ልብስ ካሸተተ በኋላ እንዲህ ብሎ መረቀው፤ “እነሆ፤ የልጄ ጠረን፣ እግዚአብሔር እንደ ባረከው፣ እንደ መስክ መዐዛ ነው።
እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “ይህ ሕፃን በእስራኤል ለብዙዎች መውደቅና መነሣት ምክንያት እንዲሆን፣ ደግሞም ክፉ ለሚያስወሩበት ምልክት እንዲሆን ተወስኗል፤