ዘፍጥረት 27:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው፤ ይሥሐቅ የያዕቆብን ልብስ ካሸተተ በኋላ እንዲህ ብሎ መረቀው፤ “እነሆ፤ የልጄ ጠረን፣ እግዚአብሔር እንደ ባረከው፣ እንደ መስክ መዐዛ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እርሱም ቀረበ፥ ሳመውም፥ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፥ ባረከውም፥ እንዲህም አለ፦ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብን ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፥ “እነሆ የልጄ መልካም ሽታ፥ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሱም ቀረበ፤ ሳመውም፤ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፤ ባረከውም፤ እንዲህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እርሱም ቀረበ ሳመውም የልብሱንም ሽታ አሸተት ባረከውም እንዲህም አለ፦ የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፤ |
በዚህ ጊዜ እስራኤል ዐይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ ዐቀፋቸው።
ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤ “አባቶቼ አብርሃምና ይሥሐቅ በፊቱ የተመላለሱት እግዚአብሔር፣ ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስ በዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ፣
ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦ “እግዚአብሔር ምድሩን ይባርክ፤ ድንቅ የሆነውን ጠል ከላይ ከሰማይ በማውረድ፣ ከታች የተንጣለለውን ጥልቅ ውሃ