ዘፍጥረት 24:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም ጌታዬን፣ ‘ሴቲቱ ከእኔ ጋራ ወደዚህ ለመምጣት ባትፈቅድስ?’ ብዬ ጠየቅሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታዬንም፦ ‘ሴቲቱ ምናልባት ባትከተለኝሳ?’ አልሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ጌታዬን ‘ልጅቷ ከእኔ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ ምን ላድርግ?’ ብዬ ጠየቅሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታዬንም ሴቲቱ ምናልባት ከእኔ ጋር መምጣትን ባትፈቅድስ አልሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታዬንም፦ ሴቲቱ ምናልባት ባትከተለኝሳ? አልሁት። |
አገልጋዩም፣ “ሴቲቱ ከእኔ ጋራ ወደዚህ ምድር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆን ምን አደርጋለሁ? ልጅህን አንተ ወደ መጣህበት አገር ልውሰደውን?” ሲል ጠየቀው።