ዘዳግም 7:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥህን ሕዝቦች ሁሉ ማጥፋት አለብህ፤ አትዘንላቸው፤ ወጥመድ ስለሚሆኑብህም አማልክታቸውን አታምልክ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ የሚጥላቸውን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋቸዋለህ፥ ዓይንህም አታዝንላቸውም፤ ወጥመድ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእጅህ ላይ የጣለልህን ሕዝቦች ሁሉ ያለ ርኅራኄ ደምስስ፤ ጣዖቶቻቸውንም ለማምለክ ወጥመድ ውስጥ አትግባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የአሕዛብ ምርኮ ትበላለህ፤ ዐይንህም አታዝንላቸውም፤ ያም ለአንተ ክፉ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህም እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ የሚጥላቸውን አሕዛብን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ፤ ዓይንህም አታዝንላቸውም፤ ያም ወጥመድ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው። |
ከዚያ በኋላ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን፣ ከመቅሠፍት፣ በከተማው ከሰይፍና ከራብ የተረፈውንም ሕዝብ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ሕይወታቸውን ለማጥፋት ለሚሹ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፤ አይራራላቸውም፤ አይምራቸውምም።’
“ ‘የምድሪቱን ነዋሪዎች አሳድዳችሁ ሳታስወጧቸው ብትቀሩ ግን፣ እንዲኖሩ የተዋችኋቸው ሰዎች ለዐይናችሁ ስንጥር፣ ለጐናችሁም እሾኽ ይሆኑባችኋል፤ በምትኖሩበትም ምድር ችግር ይፈጥሩባችኋል።
አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ አሳልፎ በሰጠህና አንተም ድል ባደረግሃቸው ጊዜ፣ ሁሉንም ፈጽመህ ደምስሳቸው፤ ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፤ አትራራላቸውም።
የአማልክታቸውን ምስሎች በእሳት አቃጥል፤ በላያቸው የሚገኘውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ ለራስህ አታድርግ፤ አለዚያ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ስለ ሆነ ያሰናክልሃል።
እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ ያለ አንዳች ርኅራኄ ፈጽሞ ይደመስሳቸው ዘንድ እስራኤልን እንዲወጉ ልባቸውን ያደነደነው ራሱ እግዚአብሔር ነውና።
ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም። እግዚአብሔርንም አስቈጡት፤
ጌዴዎን በወርቁ ኤፉድ ሠራ፤ በተወለደበትም ከተማ በዖፍራ አኖረው። እስራኤልም በሙሉ ኤፉዱን በማምለክ ስላመነዘሩ፣ ኤፉዱ ለጌዴዎንና ለቤተ ሰቡ ወጥመድ ሆነ።