ዘዳግም 3:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አምላካችን እግዚአብሔር የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመላው ሰራዊቱ ጋራ ሁሉ እንደዚሁ በእጃችን ላይ ጣላቸው፤ እኛም አንድ እንኳ በሕይወት ሳናስቀር አጠፋናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ አምላካችን ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዖግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፥ እኛም አንድ ሰው እንኳ ሳናስቀርለት አጠፋነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካችን የባሳንን ንጉሥ ዖግንና ሕዝቡን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም ከእነርሱ አንድ እንኳ ሳናስቀር ሁሉንም አጠፋን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እግዚአብሔርም ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዐግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም አጠፋነው፤ አንድ ሰው እንኳን ለዘር አልቀረለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችን እግዚአብሔርም ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዐግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም መታነው፤ አንድ ሰው እንኳ አምልጦ አልቀረለትም። |
ቂጣ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ ነው።
እግዚአብሔር፣ “እርሱን፣ መላው ሰራዊቱንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለ ሰጠሁህ፣ አትፍራው፤ ሐሴቦንን ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ ያደረግህበትን በርሱም ላይ አድርግበት” አለኝ።
በዚያ ጊዜ ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ የዐግ ግዛት ከሆነው፣ በባሳን ከሚገኘው ከጠቅላላው የአርጎብ ክልል ስድሳ ከተሞች ውስጥ፣ እኛ ያልያዝነው አንድም ከተማ አልነበረም።
ይህም በአስታሮትና በኤድራይ ሆኖ የገዛውን በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት በሙሉ ያጠቃልላል፤ ዐግም በሕይወት ከቀሩት ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ ነበር። እነዚህንም ሙሴ ድል አደረጋቸው፤ ምድራቸውንም ያዘ፤
ድንበራቸው ከመሃናይም አንሥቶ ባሳንን በሙሉ ይጨምርና፣ በባሳን ያሉትን ስድሳ የኢያዕር ከተሞች ሁሉ ይዞ የባሳን ንጉሥ የዐግን ግዛት ሁሉ የሚያካትት ሲሆን፣