“በሩቅ የሚገኙትን ድንበሮች እንኳ ሳይቀር፣ መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው። የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፣ የባሳን ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።
ዘዳግም 2:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴዎንና መላው ሰራዊቱ በያሀጽ ጦርነት ሊገጥሙን በወጡ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴዎንም፥ እሱና ሕዝቡም ሁሉ፥ ሊጋጠሙን ወደ ያሐጽ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሲሖንም ያለውን ሰው ሁሉ አሰልፎ በያሐጽ ከተማ አጠገብ ከእኛ ጋር ለመዋጋት ወጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊዋጉን ወደ ኢያሳ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊጋጠሙን ወደ ያሀጽ ወጡ። |
“በሩቅ የሚገኙትን ድንበሮች እንኳ ሳይቀር፣ መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው። የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፣ የባሳን ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ።
እግዚአብሔርም፣ “እነሆ፤ ሴዎንንና አገሩን ለእናንተ አሳልፌ ልሰጣችሁ ተነሥቻለሁ፤ አሁንም እርሱን አሸንፋችሁ ምድሩን ለመውረስ ተነሡ” አለኝ።
ከዚያም ተመልሰን ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ይዘን ወጣን፤ የባሳን ንጉሥ ዐግም ከመላው ሰራዊቱ ጋራ ሆኖ በኤድራይ ጦርነት ሊገጥመን ተነሣ።
እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ የሚገኘውን የዓረባን ክፍል በሙሉ ይዞ፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ የሚዘልቀውን ግዛታቸውን የወሰዱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤