በዐሥራ አራተኛው ዓመት ኮሎዶጎምርና ከርሱ ጋራ የተባበሩት ነገሥታት ወጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፣ ዙዚምን በሃም፣ ኤሚማውያን በሴዊ ቂርያታይም፣
ዘዳግም 2:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ደግሞ በዚያ ይኖሩ የነበሩት የራፋይማውያን ምድር እንደ ሆነ ይቈጠር ነበር፤ አሞናውያን ግን ዘምዙማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ፥ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ አሞናውያን ግን ዘምዙማውያን ብለው ይጠሩአቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም [ይህም ግዛት በዚያ ይኖሩ በነበሩ ሕዝብ ይጠሩ በነበሩበት ስም የረፋያውያን ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ዐሞናውያን በበኩላቸው ዛምዙሚም ብለው ይጠሩአቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቈጠረ፤ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበረ፤ አሞናውያን ግን “ዘምዞማውያን” ብለው ይጠሩአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ፤ ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ አሞናውያን ግን ዘምዙማውያን ብለው ይጠሩአቸዋል። |
በዐሥራ አራተኛው ዓመት ኮሎዶጎምርና ከርሱ ጋራ የተባበሩት ነገሥታት ወጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፣ ዙዚምን በሃም፣ ኤሚማውያን በሴዊ ቂርያታይም፣
ዘምዙማውያን ብርቱዎች፣ ቍጥራቸው የበዛና እንደ ዔናቃውያን ቁመተ ረዣዥሞች ነበሩ፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ፊት አጠፋቸው፤ እነርሱም አሳደዷቸው፤ በምትካቸውም ሰፈሩበት።
ከራፋይማውያን ወገን የተረፈ የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ ነበር። ዐልጋው ከብረት የተሠራ ቁመቱም ዘጠኝ ክንድ፣ ስፋቱ ደግሞ አራት ክንድ ነበር። ይህም እስካሁን በአሞናውያን ከተማ በረባት ይገኛል።