የራስ ማሰሪያዎችንም አድርግላቸው፤ ከዚያም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን መታጠቂያዎችን አስታጥቃቸው፤ ክህነት የዘላለም ሥርዐት ይሆንላቸዋል። “በዚህም መንገድ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትክናቸዋለህ።
ዘዳግም 18:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ስም ቆሞ ለዘላለም ያገለግል ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጧል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ስም ቆሞ ለዘለዓለም ያገለግል ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለዘለዓለም በክህነት ያገለግሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ መካከል የሌዊን ነገድ መርጦአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ከልጆቹ ጋር በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ቁሞ ለዘለዓለም ያገለግል ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ መርጦታልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ከልጆቹ ጋር ተነሥቶ በእግዚአብሔር ስም ለዘላለም ያገለግል ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ ስለ መረጠው ነው። |
የራስ ማሰሪያዎችንም አድርግላቸው፤ ከዚያም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን መታጠቂያዎችን አስታጥቃቸው፤ ክህነት የዘላለም ሥርዐት ይሆንላቸዋል። “በዚህም መንገድ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትክናቸዋለህ።
ቆሬንና ተከታዮቹን በሙሉ እንዲህ አላቸው፤ “የርሱ የሆነውና የተቀደሰው ማን መሆኑን እግዚአብሔር ጧት ያሳውቃል፤ ወደ ራሱም ያመጣዋል፤ የሚመርጠውን ሰው ወደ ራሱ እንዲቀርብ ያደርገዋል።
በዚያ ጊዜ፣ ዛሬም እንደሚያደርገው ያገለግል ዘንድ፣ በእግዚአብሔርም ፊት እንዲቆምና በስሙ እንዲባርክ የእግዚአብሔርንም የኪዳኑን ታቦት እንዲሸከም እግዚአብሔር የሌዊን ነገድ ለየ።