ዳንኤል 11:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካሚቱንም ምድር ይወርራል፤ ብዙ አገሮች በእጁ ይወድቃሉ፤ ኤዶም፣ ሞዓብና የአሞን መሪዎች ግን ከእጁ ያመልጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውብ የሆነችውንም የተስፋይቱን ምድር ይወራል፤ ብዙ አገሮችም በእርሱ እጅ ይወድቃሉ፤ ነገር ግን የኤዶም፤ የሞአብና የዐሞን አገሮች ከወረራው ያመልጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ መልካሚቱም ምድር ይገባል፥ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ፥ ነገር ግን ኤዶምያስና ሞዓብ ከአሞንም ልጆች የበለጡት ከእጁ ይድናሉ። |
እነርሱም ግብጽ፣ ይሁዳ፣ ኤዶም፣ አሞን፣ ሞዓብና ጠጕራቸው ዙሪያውን የሚከረከም የበረሓ ነዋሪዎች ሁሉ ናቸው፤ እነዚህ ሕዝቦች ሁሉ በርግጥ የተገረዙ አይደሉምና፤ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው አልተገረዘም።”