እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
2 ጢሞቴዎስ 4:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ በዚያ ቀን ለእኔ ይሰጠኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የርሱን መገለጥ ለናፈቁ ሁሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእንግዲህም ወዲህ ጻድቅ ፈራጅ የሆነ ጌታ በዚያ ቀን ሊሸልመኝ የጽድቅ አክሊል አዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን መገለጡን በፍቅር ለናፈቁት ሁሉ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። |
እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
“እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የገዛ ገንዘቤ ይሆናሉ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “አባት የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚታደግ ሁሉ እኔም እታደጋቸዋለሁ።
በዚያ ቀን ብዙዎች፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህ አጋንንት አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ታምራት አላደረግንምን?’ ይሉኛል።
እርሱ ብቻ ሳይሆን፣ የመጀመሪያውን የመንፈስ ፍሬ ያገኘን እኛ ራሳችን የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነታችንን በናፍቆት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን።
ሥራው እንዴት እንደ ሆነ ይታያል፤ ምክንያቱም ያ ቀን ወደ ብርሃን ያመጣዋል። በእሳት ስለሚገለጥ እሳቱ የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ምንነት ይፈትናል።
ለውድድር የሚዘጋጅ ማንኛውም ሰው በሁሉም ነገር ራሱን ይገዛል፤ እነርሱ ዐላፊ ጠፊ የሆነውን አክሊል ለማግኘት ይደክማሉ፤ እኛ ግን ለዘላለም የማይጠፋውን አክሊል ለማግኘት እንደክማለን።
አሁን ግን ሞትን ደምስሶ በወንጌል አማካይነት ሕይወትንና ኢመዋቲነትን ወደ ብርሃን ባወጣው በመድኀኒታችን በክርስቶስ ኢየሱስ መምጣት ተገልጧል።
መከራን የምቀበለውም ለዚሁ ነው፤ ሆኖም ያመንሁትን እርሱን ስለማውቅ አላፍርበትም፤ የሰጠሁትንም ዐደራ እስከዚያች ቀን ድረስ መጠበቅ እንደሚችል ተረድቻለሁ።
በእግዚአብሔር ፊት እንዲሁም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ባለው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ መገለጡንና መንግሥቱን በማሰብ ይህን ዐደራ እልሃለሁ፤
ክርስቶስ የብዙ ሰዎችን ኀጢአት ለመሸከም፣ እንዲሁ አንድ ጊዜ መሥዋዕት ሆኗል፤ ሁለተኛ ጊዜም ይገለጣል፤ ይህም ለሚጠባበቁት ድነትን ለማምጣት እንጂ ኀጢአትን ለመሸከም አይደለም።
“እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሳይቀሩ፣ ዐይን ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ።” አዎ! ይህ ሁሉ ይሆናል። አሜን።
ከዚያም ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ አንድ ነጭ ፈረስ ነበረ፤ በፈረሱም ላይ፣ “ታማኝና እውነተኛ” የሚባል ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።
ሊደርስብህ ያለውን መከራ አትፍራ። እነሆ፤ ዲያብሎስ ሊፈትናችሁ አንዳንዶቻችሁን ወደ እስር ቤት ይጥላል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።
ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ይሰግዱ ነበር፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው እንዲህ ይላሉ፤
በዙፋኑ ዙሪያ ሌሎች ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በእነርሱም ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።