ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቍጥጥሩም ሥር አዋላቸው፤ ሜቴግ አማ የተባለችውንም ከተማ ከፍልስጥኤማውያን ቍጥጥር ነጻ አደረጋት።
2 ሳሙኤል 5:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ከገባዖን እስከ ጌዝር ድረስ እያሳደደ መታቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ዳዊት ጌታ እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ከገባዖን እስከ ጌዜር ድረስ መታቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጥኤማውያንንም አሸነፈ፤ ከጌባዕ አንሥቶ እስከ ጌዜር ድረስም አባረራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖንም እስከ ጌሴራ ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፥ ከገባዖንም እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መታ። |
ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቍጥጥሩም ሥር አዋላቸው፤ ሜቴግ አማ የተባለችውንም ከተማ ከፍልስጥኤማውያን ቍጥጥር ነጻ አደረጋት።
እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣ በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።
ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋራ ዐብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።