“እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ ጠል አያረስርሳችሁ፤ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቍርባን እህል የሚያበቅሉም ዕርሻዎች አይኑራቸው፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሷልና፤ የሳኦል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም።
2 ሳሙኤል 21:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ወሰደ፤ የኢያቢስ ገዦች፣ ፍልስጥኤማውያን ሳኦልን በጊልቦዓ ከገደሉ በኋላ እነርሱን ከሰቀሉት ከቤትሳን አደባባይ በድብቅ ወስደዋቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሄዶ፥ ሳኦልን በጊልቦዓ በገደሉ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ከሰቀሉአቸው ስፍራ ከቤት ሻን አደባባይ ከሰረቁት ከያቤሽ ገለዓድ ሰዎች የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ወሰደ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በገለዓድ ምድር ወደምትገኘው ወደ ያቤሽ ሕዝብ ሄዶ የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን ዐፅም አመጣ፤ የያቤሽ ሕዝብ ዐፅሙን ያገኙት ፍልስጥኤማውያን ሳኦልን በጊልቦዓ በገደሉበት ቀን ሬሳዎችን ከሰቀሉበት ከቤትሻን አደባባይ በመስረቅ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሄደ፤ ሳአልንም በጌላቡሄ በገደሉት ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ከሰቀሉአቸው ስፍራ ከቤትሳን አደባባይ ከሰረቁት ከኢያቤስ ገለዓድ ሰዎች የሳኦልን አጥንትና የልጁን የዮናታንን አጥንት ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሄደ፥ ሳኦልንም በጊልቦዓ በገደሉ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ከሰቀሉአቸው ስፍራ ከቤትሳን አደባባይ ከሰረቁት ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ወሰደ፥ |
“እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ ጠል አያረስርሳችሁ፤ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቍርባን እህል የሚያበቅሉም ዕርሻዎች አይኑራቸው፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሷልና፤ የሳኦል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም።
ወሬ ነጋሪው ወጣትም እንዲህ አለ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ የሠረገሎችና የፈረሰኞች አለቆች ተከታተሉት።
የይሁዳም ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ በዚያም ዳዊትን ቀብተው በይሁዳ ቤት ላይ አነገሡት። ሳኦልን የቀበሩት የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች መሆናቸውን ለዳዊት በነገሩት ጊዜ፣
ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።
እንዲሁም በይሳኮርና በአሴር ውስጥ ቤትሳን፣ ይብለዓም፣ የዶር ሕዝብ፣ ዓይንዶር፣ ታዕናክና መጊዶ በዙሪያቸው ካሉ ሰፈሮቻቸው ጋራ የምናሴ ነበሩ፤ ሦስተኛውም ናፎት ነው።
ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፣ “እነዚህ ሸለፈታሞች መጥተው መሣለቂያ እንዳያደርጉኝ፣ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፣ ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።