2 ሳሙኤል 20:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእስራኤል ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነኝ፤ አንተ በእስራኤል እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት ትሻለህ፤ የእግዚአብሔርን ርስት ለመዋጥ የፈለግኸው ለምንድን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤል ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነኝ፤ አንተ በእስራኤል እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት ትሻለህ፤ የጌታን ርስት ለመዋጥ የፈለግኸው ለምንድን ነው?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔ ከተማ ግን ታላቅ ከተማ ናት፤ በእስራኤል ሰላም የሰፈነባትና ታማኝ ከተማ እርስዋ ናት፤ ታዲያ፥ አንተ ይህችን ከተማ ለመደምሰስ ለምን ታቅዳለህ? የእግዚአብሔር ርስት የሆነውን ነገር ለማፍረስ ትፈልጋለህን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ኀያላን ዘንድ ሰላምን ከሚወድዱት አንድዋ ነኝ፤ አንተ ግን በእስራኤል ያለችውን ከተማና እናት ከተማን ለማፍረስ ትሻለህ፤ ስለምንስ የእግዚአብሔርን ርስት ታጠፋለህ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ዘንድ ሰላምንና እውነትን ከሚወድዱ እኔ ነኝ፥ አንተ በእስራኤል ያለችውን ከተማና እናት ለማፍረስ ትሻለህ፥ ስለ ምንስ የእግዚአብሔርን ርስት ትውጣለህ? ብላ ተናገረች። |
አሁንም በፍጥነት ላኩና፣ ‘በምድረ በዳው ባለው የወንዙ መሻገሪያ እንዳታድር፤ ሳትዘገይ ፈጥነህ መሻገር አለብህ፤ አለዚያ ግን ንጉሡና ዐብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ትዋጣላችሁ’ ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት።”
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አባቶቻችንን ከግብጽ ባወጣህ ጊዜ፣ በባሪያህ በሙሴ አማካይነት እንደ ተናገርኸው ሁሉ፣ ርስትህ ይሆኑ ዘንድ ከምድር ሕዝቦች ሁሉ ለይተሃቸዋልና።”
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላን፣ አድቅቆ ፈጨን፤ እንደ ባዶ ማድጋ አደረገን፤ እንደ ዘንዶ ዋጠን፣ እንደ ጣፋጭ በልቶን ሆዱን ሞላ፤ በኋላም አንቅሮ ተፋን፤
ጠላቶችሽ ሁሉ በአንድ ላይ፣ አፋቸውን በኀይል ከፈቱ፤ ጥርሳቸውን እያፏጩ አሾፉ፤ እንዲህም አሉ፤ “ውጠናታል፤ የናፈቅነው ጊዜ ይህ ነበር፤ ኖረንም ልናየው በቃን።”
የያዕቆብን መኖሪያ ሁሉ፣ ጌታ ያለ ርኅራኄ ዋጣቸው፤ የይሁዳን ሴት ልጅ ምሽጎች፣ በቍጣው አፈረሳቸው፤ መንግሥቷንና መሳፍንቷን፣ በማዋረድ ወደ ምድር ጣላቸው።
ሁለት መቶ ዐምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከርሱ ጋራ ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤
በዚህ ድንኳን እስካለን ድረስ ከብዶን እንቃትታለን፤ ምክንያቱም ሟች የሆነው በሕይወት እንዲዋጥ ሰማያዊውን መኖሪያችንን ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ አንፈልግም።
ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይኸውም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው።
ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፣ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ እንዲህ ሲል ሳመው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶህ የለምን?
አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባሪያውን ቃል ያድምጥ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደ ሆነ፣ ቍርባን ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፤ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳድደውኛልና።