Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 18:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አብርሃምም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ ዐብረህ ታጠፋለህን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አብርሃምም ቀረበ ዓለም፦ “በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በእርግጥ በደል የሌለባቸውን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አብ​ር​ሃ​ምም ቀረበ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ጻድቁ እንደ ኃጥኡ አይ​ሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አብርሃምም ቀረበ አለም፦ በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን?

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 18:23
15 Referencias Cruzadas  

ሙሴና አሮን ግን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንድ ሰው ኀጢአት በሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?” ሲሉ ጮኹ።


ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፣ “እነሆ ኀጢአት የሠራሁትም የተሳሳትሁም እኔ ነኝ፤ እነዚህ ግን በጎች ናቸው፤ ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን” አለ።


አቢሜሌክም ገና አልደረሰባትም ነበርና እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፤ በደል ያልፈጸመውን ሕዝብ ታጠፋለህን?


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በንጹሕ ውሃ ታጥበን፣ በእውነተኛ ልብና በሙሉ እምነት ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።


ፍትሕን የሚጠላ ሊያስተዳድር ይችላልን? አንተስ ጻድቁንና ኀያል የሆነውን ትኰንናለህ?


እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”


መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤ ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤ ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤ አለዚያማ ደፍሮ፣ ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው?’ ይላል እግዚአብሔር።


ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ።


እግዚአብሔር ፍትሕን ያጣምማልን? ሁሉን ቻይ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን?


ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ተኩል ዝናብ አልዘነበም።


ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።


ዐምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ቢገኙ፣ በውኑ ነዋሪዎቹን ሁሉ ታጠፋለህን? በውስጧ ለሚገኙ ዐምሳ ጻድቃን ስትል ከተማዪቱን ይቅር አትልምን?


ከሐሰት ክስ ራቅ፤ በደል የሌለበትን ወይም ጻድቁን ሰው ለሞት አሳልፈህ አትስጥ፣ በደለኛውን ንጹሕ አላደርግምና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios