2 ሳሙኤል 17:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መተኛ ምንጣፎች፣ ወጭቶችና የሸክላ ዕቃዎች ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ስንዴና ገብስ፣ ዱቄትና የተጠበሰ እሸት፣ ባቄላና ምስር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መተኛ ምንጣፎች፥ ወጭቶችና የሸክላ ዕቃዎች ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ስንዴና ገብስ፥ ዱቄትና የተጠበሰ እሸት፥ ባቄላና ምስር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ምንቸቶችንና የሸክላ ማሰሮዎችን፥ የመኝታ አልጋዎችንም ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ለዳዊትና ለተከታዮቹ የሚሆን ስንዴ፥ ገብስ፥ ዱቄት፥ የተጠበሰ እሸት፥ ባቄላ፥ አተር፥ ማር፥ አይብ፥ እርጎና በጎችን አመጡ፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት ዳዊትና ተከታዮቹ በበረሓ ኑሮ እንደሚርባቸው፥ እንደሚጠማቸውና እንደሚደክማቸው በማሰብ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሥር አልጋዎችና ምንጣፎች፥ ዐሥርም ጋኖችና ፊቀኖች፥ የስንዴና የገብስ ዱቄት፥ ስልቅ አተርና ምስር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቦአል፥ ደክሞአል፥ ተጠምቶአል ብለው ምንጣፍ፥ ዳካ፥ የሸክላም ዕቃ፥ ይበሉም ዘንድ |
አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥ የምትኖር፣ መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ ለራስህም፣ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።
አቢግያም ጊዜ አላጠፋችም፤ ሁለት መቶ እንጀራ፣ ሁለት አቍማዳ የወይን ጠጅ፣ ዐምስት የተሰናዱ በጎች፣ ዐምስት መስፈሪያ የተጠበሰጠ እሸት፣ መቶ የወይን ዘለላና ዘቢብ፣ ሁለት መቶ ጥፍጥፍ የበለስ ፍሬ ወስዳ በአህዮች ላይ ጫነች።