ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ እነዚህ ሁለቱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሥ ዳዊትም፣ “አኪጦፌል በአንተ ላይ እንዲህ እንዲህ ብሎ ስለ መከረብህ ተነሥተህ በፍጥነት ወንዙን ተሻገር” አሉት።
2 ሳሙኤል 17:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኩሲም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲህ አላቸው፤ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው መክሯቸው ነበር፤ እኔ ግን እንዲህ እንዲህ አድርጉ ብዬ መክሬአቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑሻይ ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲህ አላቸው፥ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች እንዲህ እንዲህ አድርጉ ሲል መክሮአቸው ነበር፤ እኔ ግን እንዲህ እንዲህ አድርጉ ብዬ መክሬአቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እርሱና አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤላውያን መሪዎች የሰጡትን ምክር ሑሻይ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ነገራቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርካዊው ኩሲም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፥ “አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህና እንዲህ መክሮአል፤ እኔ ግን እንዲህና እንዲያ መክሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሲም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፦ አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህና እንዲህ መክሮአል፥ እኔ ግን እንዲህና እንዲህ መክሬአለሁ። |
ሰዎቹ ከሄዱ በኋላ እነዚህ ሁለቱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሥ ዳዊትም፣ “አኪጦፌል በአንተ ላይ እንዲህ እንዲህ ብሎ ስለ መከረብህ ተነሥተህ በፍጥነት ወንዙን ተሻገር” አሉት።